የሀገር ውስጥ ዜና

ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እና የክልሉ ካቢኔ አባላት በሰሜን ሸዋ ዞን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ

By Melaku Gedif

July 11, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ እና የክልሉ ካቢኔ አባላት በሰሜን ሸዋ ዞን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ በሰሜን ሸዋ ዞን ደረጃ ከ270 ሚሊየን በላይ ችግኝን ለመትከል እንደታቀደና በዞን ደረጃ በሐምሌ ስድስት በአሳግርት ወረዳ በአንድ ጀንበር 48 ነጥብ 6 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱ ተመላክቷል፡፡

የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ኤልያስ አበበ÷ በዛሬው ዕለት የዚሁ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ እቅድ አካል ርዕሰ መስተዳድሩ እና ካቢኔያቸው በባሶና ወረና ወረዳ ደበሌ ቀበሌ የችግኝ ተከላ ማከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የደበሌ ቀበሌ ማህበረሰብ ፣ የዞኑ አመራር እንዲሁም የባሶና ወረና ወረዳ አመራሮች መሳተፋቸውን ከደብረብርሃን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!