አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ የተገነባው አምቦ ኢፋ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተመረቀ።
ትምህርት ቤቱን መርቀው የከፈቱት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሺመልስ አብዲሳ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ናቸው።
ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቱ በአምቦ እና አካባቢዋ ከሚገኙ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን አወዳድሮ የሚቀበል ሲሆን ፥ ተማሪዎችን በተግባር በታገዘ ትምህርት እንደሚያስተምር ተገልጿል።
ተማሪዎቹ በተጨማሪም ሌሎች ዓለም አቀፍ ቋንቋዎችንም ይማራሉም ነው የተባለው።
በዘመን በየነ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!