የሀገር ውስጥ ዜና

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መህሙድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኤርትራ ገቡ

By Alemayehu Geremew

July 09, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መህሙድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ኤርትራ አስመራ ገብተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መህሙድ÷የኤርትራ አቻቸው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባቀረቡላቸው ግብዣ መሰረት ነው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ ያመሩት፡፡

የሶማሊያ አዲሱ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መህሙድ አስመራ ሲደርሱም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በኤርትራ ቆይታቸውም ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡