Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

1443ኛው የኢድ አልአድሀ (አረፋ) በአፋር ክልል በአል በድምቀት ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1443ኛው የኢድ-አልአድሀ (አረፋ) በአል በአፋር ክልል ሰመራን ጨምሮ በዱብቲ፣ በሎግያ እና በተለያዩ የክልሉ ከተሞች እና አካባቢዎች በድምቀት ተከብሯል፡፡
በበዓሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች እና ተከታዮች በተገኙበት ነው የተከበረው፡፡
በበአሉ የተገኙ የሃይማኖቱ አባቶች እንደገለጹት÷ በዓሉ ለመላው የሙስሊሙ ማህበረሰብ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እንዲሆን መመኘታቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡
የተቸገሩ ወገኖቻችን እና ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን በመርዳት የምናሳልፈው በአል ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version