Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳት ሊሆን ይባል- የሃይማኖት አባቶች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳት ሊሆን ይባል ሲሉ የእስልምና ሃይማኖት አባቶች ገለጹ፡፡
1443ኛው ዓመተ ሂጅራ ዒድ አል አድሃ (ዐረፋ) በዓል በደሴ ከተማ ፉርቃን መስጅድ በድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ የተገኙት የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ÷ ሕዝበ ሙስሊሙ በመተባበርና በመደጋገፍ በአሉን ሊያከብር እንደሚገባ ጠቁመው÷ ጥላቻን በመሻርና በፍቅር በመገንባት ሀገርን ማሻገር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በአሉ ድጋፍ የሚሹትን የምንረዳበት እሴቶቻችን የምናስቀጥልበት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በጎ እሴቶችን በማስቀጠል ማህበረሰቡ መረዳዳቱን እና መተዛዘኑን ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባዋል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በበአሉ በርካታ ቁጥር ያለው ምእመን ወደ ደሴ ፉርቃን መስጂድ በማምራት በአንድነትና በህብረት ለፈጣሪያቸው ጸሎትና ምስጋና አድርሰዋል፡፡
የሶላት ስነ ሰርአቱን የመሩት የሃይማኖት አባቶች መተጋገዝ መደጋገፍና መረዳዳት ከየትኛውም ጊዜ በላይ የሚያስፈልገን ሰዓት ነው ብለዋል፡፡
ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳት ሊሆን እንደሚገባም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በከድር መሀመድ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version