አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1443ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ተከብሯል፡፡
በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ ትንሿ ስተዲየም የእምነቱ ተከታዮች በሶላት ስነ አክብረዋል።
በስነ ስርዓቱ ላይ ተክቢራን ጨምሮ የተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ተካሂደዋል።
በዓሉን አስመልክቶ የእስልምና ሀይማኖት አባቶች ሀጂ ሙፍቲ ዑመር ኢድሪስ እና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ባስተላፉት መልዕክት፥ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሀ /አረፋ/ በዓልን አቅመ ደካሞችን በማገዝና በመጠየቅ እንዲያሳልፍ ጥሪ አቅርበዋል።
ታላቁ የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል በፍቅር፣ በአንድነትና በወንድማማችነት እንዲከበር ህዝበ ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ አንድነቱንና ወንድማማችነቱን መጠበቅ አለበት ብለዋል፡፡