የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ከኢኮዋስ አባል ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

July 08, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ከምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) አባል ሀገራት አምባሳደሮች ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

አምባሳደር ተስፋዬ ከአምባሳደሮቹ ጋር በሁለትዮሽ ፣ ቀጣናዊ ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው ለአምባሳደሮቹ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ፥ በቀጣይ ኢትዮጵያ ከምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) አባል ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ አጠናክራ መቀጠል በሚያስችላት ጉዳዮች ላይም ነው መከሩት።

አምባሳደሮቹም አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው በመሾማቸው የእንኳን ደስ አለዎት ብለዋቸዋል ።

ውይይቱም በጋራ መግባባትና ቀጣይ አብረው በሚሰሩባቸው ሁኔታዎች ላይ በማተኮር መጠናቀቁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!