የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 204 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Alemayehu Geremew

July 08, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስተኛው ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ስራ 1 ሺህ 204 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ከተመለሱት ውስጥ 728 ወንዶች፣ 169 ህጻናት እና 307 ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ቁጥራቸው 48 ሺህ 612 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል ነው የተባለው፡፡