ዓለምአቀፋዊ ዜና

የጃፓን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገቡ

By Mekoya Hailemariam

July 08, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)   የጃፓን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገቡ።

አቤ፥  ናራ በተባለች ከተማ  የአንድ እጩ ቅስቀሳ ላይ ንግግር በማድረግ ላይ እያሉ ነው ከኋላ በጥይት የተመቱት።

የዓይን እማኞች ሺንዞ አቤ ከኋላቸው እንደተመቱ ወዲያው እንደወደቁ እና ደም ይፈሳቸው እንደነበር ተናግረዋል።

በፍጥነት ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት በዚያው ጥብቅ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ተመልክቷል።

ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠረው ግለሰብም ከእነ መሳሪያው ወዲያው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

የ67 ዓመቱ ሺንዞ አቤ ጃፓንን ለበርካታ ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት መርተዋል።

ከጤና እክል ጋር በተያያዘ በፈረንጆቹ 2020 ነበር ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁት።

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ