Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ስልጣን ለመልቀቅ ወሰኑ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 30፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ስልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሰልጣን ለመልቀቅ የወሰኑት ባለፉት ሁለት ቀናት ከ50 በላይ የመንግሥታቸው ሚኒስትሮች እና የስራ ሀላፊዎች ስልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪነታቸው ለመልቀቅ የተስማሙ ሲሆን፥ ቀጣዩ የፓርቲው መሪ እስከሚታወቅ ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው እንደሚቆዩም ተገልጿል።

እሳቸው ግን ለተወሰኑ ወራት በጠቅላይ ሚኒስትር የመቆየት ፍላጎት እንደነበራቸው ነው የሚነገረው።

የተቃዋሚው ሌበር ፓርቲ መሪ ኬይር ስታርመር የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ ለሀገሪቱ መልካም ዜና ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦  ቢቢሲና ዘ ጋርድያን

Exit mobile version