አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ዓመታዊውን የንባብ ቀን መርሐ ግብር በአብርሆት ቤተ መጻሕፍት እያካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አበረ አዳሙ ባደረጉት ንግግር÷ ሰኔ 30 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንባብ ቀን ሆኖ እንዲታወጅ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ከምክር ቤቱም በጎ ምላሽ ማግኘታቸውን ጠቅሰው÷ የንባብ ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ በመምጣቱ ግደል ሲባል ለምን የማይል ትውልድ ተፈጥሯል ነው ያሉት፡፡
ይህንን ትውልድ መቀየር የምንችለው ደግሞ በንባብ ነውም ብልዋል፡፡
መርሐ ግብሩ በተለይ ትምህርት ቤቶች በሚዘጉበት ወቅት ወጣቶች ጊዜያቸውን አልባሌ ቦታ ላይ ከማሳለፍ ይልቅ መጻሕፍትን በማንበብ እንዲያሳልፉ ለማበረታታት እና አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር ያለመ መሆኑንም አስረድተዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ደራስያን፣ አንባቢያን እና ሌሎችም የተገኙ ሲሆን÷ ደራስያን እና አንባቢያን ለታዳሚዎች የንባብ ልምዳቸውን እና ክህሎታቸውን ለታዳሚዎች አካፍለዋል፡፡
በአብርሀም ፈቀደ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!