የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያን የደኅንነት እና የሚስጥራዊ ህትመት ኢንዱስትሪ ማዕከል ማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ሠነድ ተፈረመ

By Alemayehu Geremew

July 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚስጥራዊ መለያ እና የክፍያ መፈጸሚያ ሥርአት አገልግሎት ሰጪ ከሆነው ከጃፓኑ ቶፓን ጋር የመግባቢያ ሠነድ ተፈራርመዋል፡፡

ኩባንያው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚስጥራዊ መለያ እና የክፍያ መፈጸሚያ ሥርአት አገልግሎት ሰጪ ከሆኑ ድርጅቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀስ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ማሞ ምህረቱ አስታውቀዋል፡፡

ከኩባንያው ጋርም በቀጣይ ኢትዮጵያን የደኅንነት እና የሚስጥራዊ ህትመት ኢንዱስትሪ የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙንም ጠቁመዋል።

ቶፓን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ14 ቢሊየን ዶላር በላይ በሆነ የገቢ መጠን የሚንቀሳቀስ እና በ20 ሀገራት የሚሠራ ኩባንያ ነው።