ዓለምአቀፋዊ ዜና

የአፍሪካ አየር መንገዶች በነዳጅ ዋጋ መናር 4 ቢሊየን ዶላር እንደሚያጡ ተነገረ

By Alemayehu Geremew

July 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው ዓመት የአፍሪካ አየር መንገዶች በነዳጅ ዋጋ መናር ምክንያት ማግኘት የነበረባቸውን 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ እንደሚያጡ የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር ገልጿል፡፡

የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ተከትሎም የኬንያ አየር መንገድ የበረራ ክፍያውን እንደገና ለመከለስ እንደሚገደድ ነው ማኅበሩ ያመላከተው፡፡

የአፍሪካ አየር መንገዶች በተያዘው ዓመት የሚያጡት የ4 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ገቢ በፈረንጆቹ 2019 ላይ ካስገቡት ገቢ 23 ነጥብ 4 በመቶ ያህሉን እንደሚሆን መገለጹንም ዘ ኢስት አፍሪካ ዘግቧል፡፡