ዓለምአቀፋዊ ዜና

አብዱል ፈታ አል ቡርሃን የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት የሲቪል አባላትን ከስራ አሰናበቱ

By Mikias Ayele

July 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታ አልቡርሃን የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት የሲቪል አባላትን ከስራ ማሰናበታቸው ተገለፀ፡፡

ምክር ቤቱ በቴሌግራም ገፁ እንዳስታወቀው ሊቀ መንበሩ አምስት የሉዓላዊ ምክር ቤቱን የሲቪል አባላት ከስራ ማገዳቸውን አስታውቋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል አል ቡርሃን ቀደም ሲል ከሲቪል ተቃዋሚዎች ጋር ያለውን አለመግባባት ለመቅረፍ የሱዳን ወታደራዊ አመራሮች በውይይቱ ሂደት ውስጥ እንደማይሳተፉ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም አል ቡርሀን በሱዳን ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ እና አብዮታዊ ቡድኖች የሽግግር መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ውይይት እንዲጀምሩ ጥሪ ማቅረባቸውን አረብ ኒውስ ዘግቧል፡፡