የሀገር ውስጥ ዜና

ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ከወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር ተወያዩ

By Alemayehu Geremew

July 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ከወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር ተወያይተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጽሕፈት ቤታቸው ከወጣቶቹ ጋር በነበራቸው ቆይታ በሚሄዱበት ሁሉ አንድነትን እንዲሰብኩና በጎ እንዲሰሩ አሳስበዋቸዋል።

ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹ ከሐዋሳ ከተማ ወጣቶች እና ታዳጊዎች ጋር በመሆን የችግር ተከላ፣ የከተማ ፅዳት እና የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ማከናወናቸውንም ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሌላ በኩል ርዕሰ መስተዳድሩ ከፊንላንድ አምባሳደር ኦቲ ሆሎፓይነን ጋር በትምህርት፣ በንጹሕ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት እና በአካል ጉዳተኞች ላይ በጋራ ለመሥራት መወያየታቸውም ተገልጿል፡፡

በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በትኩረት በመስራት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰሩም ነው ሥምምነት ላይ የደረሱት፡፡