የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ከሚሽን ለ3 የግብርና ምርቶች እውቅና ሰጠ

By Mikias Ayele

July 06, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ29፣ 2014 (ኤፍ  ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ከሚሽን ለአርባ ምንጭ ሙዝ፣ ለአዊ ድንች እና ለጨንቻ አፕል ምርቶች የመለያ እውቅና ሰጥቷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የግብርና ምርቶቹ በአገር አቀፍ ገበያ በስፋት ተደራሽ የመሆን ትልቅ አቅም ያላቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ይሁን እንጂ   አሁን ላይ ምርቶቹ በደካማ የግብይት ትስስር እና በገበያ መሰረተ ልማት እጦት ተደራሽ ሳይሆኑ መቅረታቸው ተጠቁሟል፡፡

በተለይም በእሴት ሰንሰለት ውስጥ ጥቂት ነጋዴዎችና ደላላዎች ገበያውን በመቆጣጠር የተዛባ የግብይት ስርዓት በመፍጠር አምራቹንም ሆነ ሸማቹን ተጠቃሚ ሳያደርጉ መቆየታቸው ነው የተገለጸው፡፡

የምርቶቹ  እውቅና መሰጠትም በክልሎቹ  የሚመረተውን  የሙዝ፣ አፕልና ድንች ምርት በብዛትና በጥራት በማምረት ያለውን ሰፊ የገበያ ተደራሽነት ለመጠቀምና የተዛባውን የገበያ ስርዓት ለማሻሻል እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡

በማህሌት ተ/ብርሃን