Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሶማሌ ክልል የ2014 ዓ.ም የመንግሥት ሴክተር መሥሪያ ቤቶችን የስራ አፈፃፀም እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል መንግሥት በ2014 ዓ.ም የመንግሥት ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ማካሄድ ጀመረ፡፡
ግምገማው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድን ጨምሮ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን፣ የሶማሌ ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ እንዲሁም የሁሉም መስሪያ ቤቶች እና የዞን አመራሮች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ግምገማውን ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ሁሉም በስራውና በዕቅድ አፈፃፀሙ እንደሚገመገም ጠቁመዋል።
የግምገማው ውጤትም ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ማለታቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የፋይናንስ አጠቃቀም፣ የፕሮጀክቶች አፈፃፀምና ሁሉም ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ለድርቅ አደጋው የሰጡት ምላሽ በዋነኛነት በግምገማው ላይ ትኩረት እንደሚደረግባቸው ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version