Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጣሊያን በሰሜናዊ የሀገሪቷ ክፍል የድርቅ አደጋ መከሰቱን ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣሊያን በሀገሪቷ ሰሜናዊ ክፍል በ70 ዓመታት ታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ድርቅ በመመታቷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለች፡፡

ድርቁ የተከሰተው ቀደም ሲል የሀገሪቷን አንድ ሦስተኛውን የግብርና ምርት አቅርቦት ይሸፍን በነበረው የ ”ፖ“ ወንዝ አካባቢ ነው ተብሏል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሞቃታማ እና ደረቅ የዓየር ንብረት ባስከተለው ድርቅ ለተጎዳው ማኅበረሰብ እና ተቋማት ውሃ በየቤቱ ለማድረስ እና ሁኔታዎችን ለመቋቋም የሀገሪቷ መንግስት ተጨማሪ ገንዘብ እና ኃይል እንዲያሰባስብ ያግዘዋል ነው የተባለው።

የ”ፖ” ወንዝ የጣሊያን ረጅሙ ወንዝ ሲሆን በአሁኑ ወቅት መድረቁ እና የሀገሪቷ አርሶ አደሮች መቸገራቸው ነው የተመለከተው፡፡

የጣሊያን መንግስት በ”ፖ” ወንዝ አካባቢ በደረሰው ድርቅ ተጎጂ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለመሆን ካወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተጨማሪ በአምስት ተጨማሪ ድርቁ ያሰጋቸዋል ባላቸው የሀገሪቷ ሰሜናዊ ክፍሎችም ተደራሽ ለመሆን 38 ሚሊየን ዶላር መድቦ እየሠራ መሆኑን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ ለተከሰተው የድርቅ አደጋ ምላሽ አስተባባሪ ኮሚሽነር ለመሾም እያሰቡ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version