Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በክልሉ የተለያዩ ማዕድናት ለምተው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች ውጤት አስመዝግበዋል- አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለይም ከለውጡ ወዲህ ወርቅን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ ማዕድናት ለምተው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ለማስቻል የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ፡፡
በክልሉ በማዕድን ዘርፍ ተሰማርተው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ለልዩ አነስተኛ ወርቅ አምራቾችና አዘዋዋሪዎች የዕውቅና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በእውቅና መርሐ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንንን ጨምሮ ምክትል አፈ ጉባዔ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ፣ የማዕድን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ናስር መሃመድ እንዲሁም የክልልና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በተለይም ከለውጡ ወዲህ ወርቅን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ ማዕድናት ለምተው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ ለማስቻል የተወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች ውጤት እያስመዘገቡ ነው ብለዋል፡፡
እነዚሁ እርምጃዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የማዕድን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ናስር መሃመድ እንደገለጹት÷ ለወርቅ አምራቾችና አዘዋዋሪዎች የተሰጠው ዕውቅና አሁን እየተገኘ ያለውን ውጤት የበለጠ ለማጠናከር ያለመ ነው።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version