ስፓርት

አትሌት ሰምበሬ ተፈሪ በአሜሪካ አትላንታ በተደረገ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አሸነፈች

By Mikias Ayele

July 04, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሰምበሬ ተፈሪ በአሜሪካ አትላንታ በተደረገ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር ቀዳሚ በመሆን አሸንፋለች፡፡

አትሌቷ ርቀቱን 30 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው  ቀዳሚ ሆና የጨረሰችው፡፡

በውድድሩ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጀማል ይመር በወንዶች  ምድብ በተመሳሳይ ርቀት 3ኛ በመሆን ማጠናቀቁን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡