የሀገር ውስጥ ዜና

በጅማ ዞን በ2 ቢሊየን ብር የተገነቡ ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው

By Meseret Awoke

July 04, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን በ2 ቢሊየን ብር የተገነቡ 229 ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ይገኛል።

ፕሮጀክቶቹ መንገድ፣ ድልድይ፣ ትምህርት ቤቶችና ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው እንደሆኑ ተመላክቷል።

በሚኒስቴር ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ፥ በዞኑ ቶባ ወረዳ በ40 ሚሊየን ብር ሲገነባ የነበረውን ኤፎ ያጪ ኢፈ ቦሩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስመርቀዋል።

ዶክተር ቢቂላ በዚህ ወቅት እንዳሉትም ፥ ሀገራችን በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ሆና እንኳን መንግስት የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።

በተለያዩ አካባቢዎች እየተመረቁ ያሉ ፕሮጀክቶች የዚሁ ማሳያ መሆኑን የጠቆሙትተ ዶክተር ቢቂላ ፥ በቀጣይም የህብረተሰቡን ችግር ከመሰረቱ ለሚፈቱ ፕሮጀክቶች ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ትጃኒ ናስር፥ ፕሮጀክቶቹ በተሰጣቸው ልዩ ትኩረት በተያዘላቸው ጊዜ መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።

በሙክታር ጠሃ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!