Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

“የሰላም ጉዳይ ለማንም የውጪ እና ባእድ አካል አሳልፈን የማንሰጠው ጉዳይ ነው” – አቶ ግርማ የሽጥላ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “የሰላም ጉዳይ ለማንም የውጪ እና ባእድ አካል አሳልፈን የማንሰጠው ጉዳይ ነው” ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ ተናገሩ።
በምዕራብ ጎጃም ዞን የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ውይይት በፍኖተ ሰላም ከተማ እየተካሄደ ነው።
አቶ ግርማ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሕግና ስርዓትን በማስፈን ለልማት እና መልካም አስተዳደር እውን መሆን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የተሟላ እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ ያለመ ሕግ የማስከበር ሥራ መተግበር ከጀመረ ወዲህ በርካታ ውጤቶች ታይተዋል ብለዋል፡፡
የምዕራብ ጎጃም አርሶ አደሮች በህልውና ትግሉ ወቅት ያደረጉትን ተጋድሎ ጠቅሰው÷ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በነበረው የሕግ ማስከበር ስራ ብዙ ነገሮች በውይይትና በንግግር እንዲፈቱ መደረጉንም አመላክተዋል፡፡
የሕግ ማስከበር ስራውም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው አቶ ግርማ ያስታወቁት፡፡
የውስጥ ጥንካሬያችንን እና የመጡ ለውጦች እንዲሁም የታዩ ጉድለቶችን መርምሮ በቀጣይ ፓርቲያችን እና የሚመራው መንግስት የሕዝባችንን ሰላም ለማረጋገጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ትንፋሻችንን ሰብሰብ አድርገን የዳገቱን የመጨረሻ ጫፍ በመውጣት ላይ ስለሆን÷ ፈተናዎችን ተቋቁመን አንድነታችንን ማጠናከር አለብን ማለታቸውን የብልጽግና ፓርቲ የአማራ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version