Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በባህላችን የተመረቀ ሰው ለበጎ የተጠራ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህላችን የተመረቀ ሰው ለበጎ የተጠራ በመሆኑ እያንዳንዱ ተመራቂ የተጠራለት ተግባር ለሀገሩ ዕድገት ምሦሶ መሆን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው በኩል ለዘንድሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው፥ እያንዳንዱ ተመራቂ ለሀገሩ ዕድገት ምሦሶ መሆን፤ ፈጠራን ለማቀላጠፍ፣ ለማኅበረሰብ ተግዳሮቶች መፍትሔዎችን ለማግኘት እና ለብዙዎች የተስፋ ብርሃን ለመሆን ሊሠራ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version