Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ጀግኖች ደማቸውን ሰጥተው ያስከበሯትን ሀገር በመስዋዕትነት እናስቀጥላለን – የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የሰራዊት አባላት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀግኖች ደማቸውን ሰጥተው ያስከበሯትን ሀገር በመስዋዕትነታችን እናስቀጥላለን ሲሉ በሰሜን ምዕራብ ዕዝ የሚገኙ ሜካናይዝድ እና የእግረኛ ክፍለ ጦር የሰራዊት አባላት ተናገሩ፡፡
በክፍለ ጦሩ የሚገኘው የ2ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሻለቃ አለምነው ተፈራ እንደገለጹት÷ ሰራዊቱ ተልዕኮውን እና አላማውን በሚገባ የሚያውቅ፣ በወታደራዊ ስነ ምግባር የተገነባ በመሆኑ ማንኛውንም ግዳጅ የሚፈፅመው አሰራሩን እና ደንቡን በመከተል ነው፡፡
ሰራዊቱ ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብን በሚገባ እንዲላበስ በስልጠና በማብቃት÷ የሀገሩን ሉዓላዊነት በመስዋትነቱ የሚያስከብር አመራርና አባላት ፈጥረናል ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያን ድንበር ለመድፈር እና ሰላሟን ለማወክ የሚሯሯጡ የውጭም ይሁን የውስጥ ፀረ ሰላም ኃይሎችን ለመደምሰስ÷ ሰራዊቱ ከምንጊዜውም በላይ በአስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
በሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የአየር መቃወሚያ ምክትል አዛዥ ሻለቃ መኳንንት ደርብ በበኩላቸው÷ የሜካናይዝድ አባላቱ ከእግረኛ ክፍለ ጦር ጋር በመቀናጀት የሀገር ሉዓላዊነት እንዳይደፈር ሌት ተቀን ዝናብና ብርዱ ሳይበግራቸው የግዳጅ ቀጣናቸውን እየጠበቁ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የሰራዊቱ አባላት በሰጡት አስተያየት÷ ጀግኖች ደማቸውን ሰጥተው ያስከበሯትን ሀገር በእኛ መስዋትነት ተከብራ እንድትቀጥል በማንኛወም ጊዜ የሚሰጠንን ግዳጅ በድል ለመወጣት ዝግጁ ነን ብለዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version