የሀገር ውስጥ ዜና

የፋና ኤፍ ኤም 98 ነጥብ 1 ማረፊያ የመዝናኛ መሰናዶ አንደኛ አመቱን አከበረ

By Meseret Awoke

July 02, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋና ኤፍ ኤም 98 ነጥብ 1 ማረፊያ የመዝናኛ መሰናዶ አንደኛ አመቱን አከበረ።

የመሰናዶው አንደኛው አመት የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው እና ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አቤል አዳሙ እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በተገኙበት ተከብሯል።

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው ፋና በሁሉም ዘርፎች የአድማጭ ተመልካቹን እርካታ ለመጨመር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አቤል አዳሙ በበኩላቸው ፋና፥ እንደማረፊያ ያሉ መሰናዶዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል አድማጮቹን የሚያከብር ስራ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

መሰናዶው ባለፉት 52 ሳምንታት እጅግ አስተማሪ የሆኑ ከ312 በላይ ፕሮግራሞችን አየር ላይ ያዋለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 180 ያህሉ በሀገር ውስጥ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ነበሩ፡፡

በአማካይ በማረፊያ እስከ ስድስት ፕሮግራሞች በየሳምንቱ አየር ላይ የሚውሉ ሲሆን በጥቅሉ እስከ ስምንት የሚደርሱ ዝግጅቶችንም ይዞ አየር ላይ የሚያውል የመዝናኛ ፕሮግራም ነው።

ማረፊያ ቅዳሜ ከረፋድ 5 ሰአት ጀምሮ እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ድረስ የሚቆይ የሬዲዮ መዝናኛ መሰናዶ ነው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!