የሀገር ውስጥ ዜና

አላስፈላጊ ክልከላዎችንና እገዳዎችን በማንሳት የማዕድን የወጪ ንግድን እናሳድጋለን – ኢ/ር ታከለ ዑማ

By Meseret Awoke

July 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ዑማ በጌጣጌጥና በከበሩ ማዕድናት ግብይት ላይ ከተሰማሩ አምራችና ነጋዴዎች ጋር መከሩ፡፡

ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ አላስፈላጊ ክልከላዎችንና እገዳዎችን በማንሳት የማዕድን የወጪ ንግድን እንደሚያሳድጉ ገልጸዋል።

ከማዕድን የወጪ ንግድ በተለይም በጌጣጌጥና በከበሩ ማዕድናት ግብይት ላይ የተሰማሩ አምራችና ነጋዴዎች ጋር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ነው ያነሱት።

ከዚህ በፊት የነበሩትን ክልከላዎችንና እገዳዎችን በማንሳትም የግብይት ስርዐቱ በገበያ ብቻ እንዲመራ ለማድረግ ወስነናል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

በተጨማሪም ማዕድን ላኪዎች በተደራጀ መልኩ ስራቸውን ለመስራት የሚያስችላቸውን አደረጃጀቶች እንዲያመቻቹ መግባባት ላይ መደረሱን አመላክተዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!