Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደመቀ መኮንን የአቅመ ደካማ ቤቶችን እድሳት አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 በተለምዶ ሀምሌ 19 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የአቅመ ደካማ ቤቶችን እድሳት አስጀምረዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመሆን 12 ቤቶች እድሳት እንደሚያደርግ አስታውቋል።
አቶ ደመቀ መኮንን ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ አቅመ ደካሞችን ኑሯቸውን ለመጋራት በማሰብ የቤቶች እድሳቱን እንዳስጀመሩ በእድሳቱ ማስጀመሪያ ወቅት ተናግረዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኑሮ ጫና ያለባቸው አቅመ ደካሞችን በመለየት ቤቶችን የማደስ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ደመቀ ቃል ገብተዋል፡፡
የቤቶቹ የእድሳት ስራ የሚከናወነው በ5 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በቅድስት አባተ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version