ዓለምአቀፋዊ ዜና

በነሐሴ ወር የ “ኦፔክ” አባል ሀገራት እና አጋሮቻቸው የነዳጅ ምርታቸውን ለማሳደግ ተሥማሙ

By Alemayehu Geremew

June 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የነዳጅ አምራችና ላኪ ሀገራት እንዲሁም አጋሮቻቸው የሚያመርቱትን የነዳጅ መጠን በቀን በ648 ሺህ በርሜል ለማሳደግ ሥምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ሩሲያ በተጣለባት ማዕቀብ ምክንያት የነዳጅ ምርቷን ለመቀነስ ተገዳ መቆየቷ የሚታወስ ሲሆን፥ “ኦፔክ” እና አጋሮቻቸው ያመቻቹትን ዕድል በማዕቀብ ያጣችውን ገቢ ለማካካስ ልትጠቀምበት ትችላለችም ነው እየተባለ ያለው፡፡

የ“ኦፔክ” አባል ሀገራትና አጋሮቻቸው ነዳጅ ላይ የተፈጠረውን የዋጋ ንረት ምርታቸውን በማሳደግ እንዲያረጋጉ ከምዕራባውያኑ ጥሪ ቀርቦላቸው ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ ውድቅ ማድረጋቸውን ሲጂቲ ኤን በዘገባው አስታውሷል፡፡