ዓለምአቀፋዊ ዜና

በጣሊያን በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 366 ደረሰ

By Feven Bishaw

March 09, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጣሊያን በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 366 ደረሰ።

በትናንትናው ዕለት ብቻም 133 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ለህልፈት ተዳርገዋል።

በሰሜናዊ ጣሊያን ብቻ 16 ሚሊየን ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን፥ ከ7 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል ነው የተባለው።

በተመሳሳይ በኢራን 49 አዲስ ሞት የተመዘገበ ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 194 ደርሷል።

በቻይና በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ተገልጿል፤ በአንድ ቀን 40 ሰዎች ብቻ ሲያዙ ይህም ከእስካሁኑ ዝቅተኛው ነው ተብሏል።

በተመሳሳይ በደቡብ ኮሪያ ከሁለት ሳምንታት ወዲህ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ነው የተገለጸው።

ሰሜን ኮሪያ ደግሞ ከኮሮና ቫይረስ ስጋት ጋር በተያያዘ በለይቶ ማቆያ እንዲቆዩ ያደረገቻቸውን 60 ያክል ዲፕሎማቶች መልቀቋን አስታውቃለች።

ምንጭ፦ ቢቢሲ እና አልጀዚራ