Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከጀርመን መንግስት የ32 ሚሊየን ዩሮ በላይ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጀርመን መንግስት የ32 ሚሊየን ዩሮ በላይ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል የፕሮግራም ስምምነት መፈረሙን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 
የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ከጀርመን የልማት ባንክ የአፍሪካ ህብረትና የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ክርስቶፍ ቲከንስ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
 
ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ከጀርመን መንግስት 32 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል የፕሮግራም ስምምነት መፈረሙን ገልጸዋል።
 
ከዚህ ባለፈም ለ20 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት 500 ሚሊየን ብር የሚገመት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ግንባታ ግብዓቶች ርክክብ መደረጉን ነው የገለጹት፡፡
 
በቀጠይ ድጋፉ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት አግባብ ላይ መወያየታቸውን አንስተው÷ የጀርመን መንግስት ላደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዳይሬክተሩ በዘርፉ የተጀመረውን የለውጥ ስራ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን÷ የራዕዩን ተሻጋሪነት በማድነቅ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል መግባታቸው ተመላክቷል፡፡
Exit mobile version