አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ 10 ሚሊየን ዶዝ ሲኖ ፋርም የተሰኘ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ ማድረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ድጋፉ በቻይና ቀዳማዊት እመቤት ፕሮፌሰር ፒንግ ሊዋን አማካኝነት በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽህፈት ቤት በኩል የተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክትር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የቻይና መንግስት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ድጋፉን ላበረከቱት የቻይና ቀዳማዊት እመቤት ፔንግ ሊዩዋን አድናቆታቸውን የገለፁት ሚኒስትሯ፥ በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ስም ለተደረገው ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን ገልፀዋል፡፡