የሀገር ውስጥ ዜና

1 ሺህ 85 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ

By Melaku Gedif

June 27, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ ችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 87 ኢትዮጵያውያን ባዛሬው ዕለት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሽ ዜጎች ውስጥም 19 የሚሆኑት ህጻናት ሲሆኑ÷ 17ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጁላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!