የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ሴቶች የሰላም ግንባታ ይፋ ማድረጊያ መርሐ ግብር ተካሄደ

By Feven Bishaw

June 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ሴቶች የሰላም ግንባታ ይፋ ማድረጊያ መርሐ ግብር ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በተገኙበት ተካሄደ፡፡

የሰላም ግንባታ ማብሰሪያ መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ በሀገራችን የተፈጠሩ ግጭቶች ንጹሀንን ህይወታቸውን አንዲያጡ ከማድረጉም በተጨማሪ ሴቶችንና ህጻናትን ለከፍተኛ ጉዳት ዳርጓል ብለዋል፡፡