Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአማራ ክልል በተወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ ውጤት መገኘቱን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በተወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ ውጤት መገኘቱን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ደሰኝ ጣሰው ገለጹ፡፡

በጎንደር ክላስተር የሚገኙ የፀጥታ አካላት በህግ ማስከበር እርምጃው እና አፈፃፀም ሁኔታ ላይ በጎንደር ከተማ ውይይት እያካሄዱ ነው።

በውይይቱ ወቅት የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ደሰኝ ጣሰው ፥ ከግንቦት ወር መጀመሪያ አንስቶ በተወሰደ ህግ የማስከበር እርምጃ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ማስፈን መቻሉን ተናግረዋል።

በተለይም በፋኖ ስም የሚነግዱ ሃይሎችን በመያዝ ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉ በክልሉ ዜጎች በነፃነት መንቀሳቀስ መቻላቸውን ነው የገለጹት።

በክልሉ ይስተዋል የነበረውን የጦር መሳሪያ ተኩስ፣ እገታ እና ዝርፊያ በተወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃ ማስቆም መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም በህገወጥ መንገድ የተገነቡ ቤቶችን ማፍረስና በመሬት ወረራ የተሰማሩ ግለሰቦች ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉን አንስተዋል፡፡

በክብረወሰን ኑሩ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version