የሀገር ውስጥ ዜና

የዴንማርክ መንግስት በኢትዮጵያ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ ለማዳረስ 10 ሚሊየን ዶላር ለገሰ

By Alemayehu Geremew

June 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዴንማርክ መንግስት በኢትዮጵያ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ በዘላቂነት ለማዳረስ የሚውል 10 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መለገሱን ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡

ዩኒሴፍ ኢትዮጵያ፥ የዴንማርክ መንግስት ላደረገው ድጋፍ ትልቅ ምሥጋና አቅርቦ ፣ ንጹሕ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር በኢትዮጵያ በዘላቂነት ለመፍታት የሚደረገውን ጥረትም ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲያግዝ መቆየቱን አስታውሷል፡፡

የዴንማርክ መንግስት በኢትዮጵያ አምባሳደር ኪራ ስሚዝ ሲንድበርግ ÷ በሶማሌ ክልል የተከሰተው ድርቅ ያሳደረውን ተጽዕኖ አውስተው በክልሉ የሚገኙ ሴቶች እና ሕፃናትን ሕይወት ለማሻሻል ንጹሕ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እጅግ አስፈላጊ ነው ማለታቸውን ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ የትዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡