የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ካውንስል ተቋቋመ

By Meseret Awoke

June 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ካውንስል በዛሬው ዕለት ተቋቁሟል፡፡

ካውንስሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ አቶ አብዱረሀማን አብደላ፣ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ሃላፊዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነው የተቋቋመው፡፡

ካውንስሉ ግብርናን በእውቀት እና በምርምር በመደገፍ ውጤታማ ማድረግን አላማ አድርጎ የተመሰረተ መሆኑን የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ አበራ ወርቁ መናገራቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኦሮሚያ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ አቶ አብዱረሀማን አብደላ በበኩላቸው ÷በክልሉ የግብርና ልማትን ለመደገፍ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት እና ሴክሬተሪያት በደንብ ቁጥር 227/2014 እንዲቋቋም መደረጉን ገልፀዋል፡፡