አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የብሔረሰቦች ምክር ቤት 3ኛ ዙር 9ኛ የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባኤው በሶስት አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ ደሬቴድ ዘግቧል፡፡
ምክር ቤቱ በመጀመሪያ የብሔረሰቦች ምክር ቤት 3ኛ ዙር 8ኛ የሥራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ- ጉባኤን አጽድቋል።
አሁን ላይም ምክር ቤቱ የ2014 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ እየተወያየ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም ጉባኤው በቆይታው የተጓደሉ ቋሚ ኮሚቴዎችንና የህገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ አባላትን እንደሚያሟላ ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!