Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለፉት ሦስት ዓመታት በጅማ ዞን የተተከሉ ችግኞች ተጨባጭ ውጤት ማሳየታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሦስት ዓመታት በጅማ ዞን የተተከሉ ችግኞች ተጨባጭ ውጤት ማሳየታቸውን ዞኑ አስታወቀ፡፡
በዞኑ ባለፉት ሦስት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ለተተከሉ ችግኞች ክትትልና ክብካቤ ሲደረግ በመቆየቱ፥ አሁን ላይ ችግኞቹ አድገው ተጨባጭ ውጤት ማሳየታቸው ነው የተገለጸው፡፡
በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርም የዞኑ ነዋሪዎች በንቃት እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር በበኩላቸው፥ የዞኑ ነዋሪዎች ችግኞችን ከመትከል ጎን ለጎን ክትትልና ክብካቤ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ጠቁመው፥ በጎርፍና በሌሎች ምክንያቶች የተጎዱ ቦታዎች ማገገማቸውን ተናግረዋል፡፡
በዘንድሮው ዓመትም ቡናን ጨምሮ በአጠቃላይ 1 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል መታቀዱንም ነው አቶ ቲጃኒ የተናገሩት፡፡
እንደ ግብርና ሚኒስቴር መረጃ፥ ለ4ኛው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከተዘጋጁት ችግኞች መካከል 52 በመቶዎቹ የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ጥረትን የሚያግዙ ናቸው፡፡
ባለፉት ሦስት ዓመታትም 18 ቢሊየን ችግኞች መተከላቸውን እና ከ80 በመቶ በላይ ያህሉ መጽደቃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያላክታል፡፡
በሙክታር ጣሃ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version