የሀገር ውስጥ ዜና

ከተፈቀደላቸው በጀት በላይ የተጠቀሙ 24 ተቋማት ተገኙ

By Meseret Awoke

June 21, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ከተፈቀደላቸው በጀት በላይ የተጠቀሙ 24 ተቋማት መገኘታቸውን የፌደራል ዋና ኦዲተር አስታወቀ።

የፌደራል ዋና ኦዲተር መስርያ ቤት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ እያቀረበ ባለው ሪፖርት በ24 መሥሪያ ቤቶች በልዩ ልዩ የሒሳብ መደቦች ሳያስፈቅዱ እና በጀት ሳያዘዋውሩ ከተደለደለው በጀት በላይ ወጪ የሆነ ሒሳብ መገኘቱን አረጋግጧል፡፡

ከመደበኛ በጀት 645 ሚሊየን 198 ሺህ ብር በላይ ሆኖ መገኘቱን ነው ያረጋገጠው።

በልዩ ልዩ የሒሳብ መደቦች ከተፈቀደላቸው በጀት በላይ ከተጠቀሙ መሥሪያ ቤቶች መካከልም ፥ የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፣ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፣ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተካተዋል።

ተቋማቱ በየሒሳብ ኮዶቹ ከተፈቀደው በጀት ከ10 በመቶ በላይ ያልተጠቀሙበትን ብቻ በመውሰድ ፤ በድምሩ ብር 21 ቢሊየን 12 ሚሊየን 778 ሺህ በላይ ብር ያልተሠራበት በጀት ተገኝቷል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!