አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳዑዲ አረቢያ በኮቪድ 19 ምክንያት በቱርክ፣ ህንድ፣ ኢትዮጵያ እና ቬትናም ላይ ጥላው የነበረውን የጉዞ እገዳ ማንሳቷን አስታውቃለች፡፡
የሀገሪቱ የዜና ተቋም ኤስ ፒ ኤ እንደዘገበው በወሩ መጀመሪያ ላይ ሳዑዲ አረቢያ በቤት ውስጥ የፊት ጭምብል ማድረግን ጨምሮ ቫይረሱን ለመከላከል የተቀመጡ ህጎችን አንስታለች፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ከሳውዲ አረቢያ ወደ ቱርክ፣ ህንድ፣ ኢትዮጵያ እና ቬትናም በሚጓዙ ዜጎቿ ላይ የተጣለው የኮሮና ቫይረስ የጉዞ እገዳ በዛሬው እለት መነሳቱን ኤስ ፒ ኤን ጠቅሶ ሬውተርስ ዘግቧል፡፡