አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በንጹሃን ዜጎች ላይ በህገወጥ እና በኢ-መደበኛ ኃይሎች የሚደርስ ጥቃት እና መተዳደሪያን ማውደም ተቀባይነት እንደሌለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ላይ ባወጡት መግለጫ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤኒንሻንጉል ጉሙዝ እና ኦሮሚያ ክልሎች፥ ዋና ዓላማቸው ኅብረተሰቡን ማሸበር በሆነ አካላት የተፈጸመው የሰው ልጆችን ህይወት የሚቀጥፍ ዘግናኝ ድርጊትን መንግስት እንደማይታገስ አስታውቀዋል።
ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰላም እና ደህንነትን መመለስ አሁንም ቅድሚያ የሚሰጠው ተግብር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።