አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ700 በላይ የሚሆኑ የስልጤ ዞን አመራሮች በዛሬው ዕለት የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱ የኢትዮጵያን ቀደምት እና አሁናዊ የታሪክ እሴቶች ለመመልከት ያስቻላቸው መሆኑን አመራሮቹ ተናግረዋል፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይት ያደረጉት አመራሮች እንደገለጹት፥ የአንድነት ፓርክ በቅብብሎሽ የመጣውን የኢትዮጵያ ቀደምት ገናናነት የሚያሳይ ነው።
ይህም የህዝቦችን አንድነት እና ሁለንተናዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ነው የገለጹት።
ፓርኩ ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና ማማ ለመውጣት የምታደርገውን ተግባር የሚያሳይ ሆኖ እንዳገኙትም ተናግረዋል።
ካለፉ ታሪኮች በመማር እና ጥሩውን እንደ ተሞክሮ በመውሰድ ወደፊት መሻገር አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በመለሰ ምትኩ