የሀገር ውስጥ ዜና

አየር መንገዱ ለ100 ሕጻናት እና ቤተሰቦቻቸው የጉዞ ወጪ ለመሸፈን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

By Alemayehu Geremew

June 16, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሕንድ ሀገር ሄደው መታከም ላለባቸው 100 የልብ ሕሙማን ሕጻናት ከእነ ቤተሰቦቻቸው የጉዞ ወጪ ለመሸፈን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

አየር መንገዱ ሥምምነቱን የፈጸመው ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን መርጃ ሕጻናት ማኅበር እና ከሮተሪ ኢትዮጵያ ጋር መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር አየር መንገዱ በሀገር ውስጥ የልብ ቀዶ ሕክምና ማድረግ ከባድ መሆኑ ለተገለጸላቸው እና ሕንድ ሀገር ሄደው መታከም ላለባቸው 100 ሕጻናት እንዲሁም ከሕጻናቱ ጋር አብረው ለሚጓዙ ተጨማሪ 100 አስታማሚዎች የጉዞ ወጪ ለመሸፈን መሥማማቱን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል።