ቴክ

ማይክሮሶፍት ከ27 ዓመታትበኋላ “ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር” መተግበሪያን ከአገልግሎት አስወጣ

By Meseret Awoke

June 16, 2022

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ማይክሮሶፍት ኩባንያ ከ27 ዓመታት በኋላ “ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር” መተግበሪያን ከአገልግሎት አስወጣ፡፡

ጎግል ክሮም፣ አፕል ሳፋሪ እና ሞዚላ ፋየር ፎክስ ገበያው ላይ ተፅዕኖ የፈጠሩ መተግበሪያዎች መሆናቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡

አሁን ላይ ዘመናዊ ስልክ፣ ላፕቶፕ እና ዴስክቶፕ ተጠቃሚዎች ከኢንተርኔት ኤክስፕሎረር ይልቅ ክሮምና ፋየርፎክስን በብዛት እንደሚጠቀሙ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

መተግበሪያው ከክሮም እና ፋየርፎክስ አንጻር ያለው ተፈላጊነት መቀነስ ከአገልግሎት እንዲወጣ ምክንያት ሆኗል ነው የተባለው።

ኩባንያው ባለፈው አመት ኢንተርኔት ኤክስፕሎረርን ከአገልግሎት ውጭ እንደሚያደርግ መግለጹ ይታወሳል።

ማይክሮሶፍትን መጠቀም እንቀጥላለን ያሉ ተጠቃሚዎችም ከዊንዶውስ10 በተጨማሪነት በፈረንጆቹ 2015 ወደ ስራ የገባውን ማይክሮስፍት ኤጅ መጠቀም ይችላሉ ነው ያለው ኩባንያው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!