Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ተቋማቱ ከ30 ሺህ በላይ መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ፣ ሪቫ ካምፕ ፋውንዴሽን እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት 30 ሺህ 703 መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት አስረክበዋል፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚንስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋኢዛ መሐመድ እንዲሁም ሪቫ ካምፕ ፋውንዴሽንን በመወከል አቶ አክሊሉ ታደሰ መጻሕፍቱን አስረክበዋል።

ሪቫ ካምፕ ፋውንዴሽን 28 ሺህ 638 መጻሕፍት ያሰባሰበ ሲሆን የአዲስ አበባ ምክር ቤት 1 ሺህ 200 መጻህፍት እንዲሁም የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ደግሞ 865 መጻህፍትን ማሰባሰባቸውንም ነው ኢዜአ የዘገበው።

መጻሕፍቱን የተረከቡት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ÷ መጻሕፍቱን ላበረከቱት ተቋማት ምሥጋና አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version