አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቀቀች።
በውድድሩ ኢትዮጵያ በ4 ወርቅ፣ 6 ብር እና 4 ነሃስ በአጠቃላይ በ14 ሜዳልያ 5ኛ ደረጃ ይዛ ማጠናቀቋን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።
በውድድሩ የመጨረሻ ቀን በሴቶች 3 ሺህ መሰናክል እና በ5 ሺህ ወንዶች ውድድር ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎችን ማግኘት ችላለች።
ከዚህ ባለፈም 2 የብር እና 1 የነሐስ ሜዳልያም በማጠናቀቂያው ቀን በሴቶች 3 ሺህ መሰናክል እና በእርምጃ ውድድር ማግኘቷ ይታወቃል።