Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ያለ አግባብ ለማትረፍ የሚሰሩ ስግብግብ ባለሀብቶችን አደብ ለማስገዛት እንደሚሰራ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 4 ፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የክልሉ መንግስት ያለ አግባብ ለማትረፍ የሚሰሩ ስግብግብ ባለሀብቶችን አደብ ለማስገዛት እንደሚሰራ  የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ፡፡

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ይህን በዱከም በግል ባለሀብት የተገነባውን ታዳሽ የብረታብረት ፋብሪካ በመረቁበት ወቅት ነው።

ርዕስ መስተዳደሩ በምረቃ ው ላይ  ባደረጉት ንግግር “የራስ ኪስ የሚያደልቡ ለሀገርና ለዜጋ ቅንጣት የማይጨነቁ ስግብግብ ባለሀብቶች በተደጋጋሚ ወደ ትክክለኛ መስመር እንዲገቡ ለማድረግ ጥረናል ከአሁን በሁኋላ ግን ትዕግስታችን አልቋል” ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የምትፈልገው ሀብታቸውን አፍስሰው ሀገር ለማቅናት የሚለፉትን እንጂ በተለያየ ቦታ ሆነው ሀብቷን የሚበዘብዙትን አይደለም ያሉት አቶ ሽመልስ፥ ሀገር እንድትቀና ከተፈለገ እነዚህ ሰዎችን አደብ ማስገዛት ያስፈልጋል ብለዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ሀገር ለማቅናት ብዙ ቢሊየን ብራቸውን የሚያፈሱ ግዙፍ ኢንዱስትሪ በመገንባት ለዜጎች የሚተርፉ ባለሀብቶች ሊበረታቱ ይገባል ነው ያሉት።

ርዕሰ መስተዳደሩ በ5  ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ካፒታል የተገነባውን ታዳሽ የብረታብረት ማምረቻ ፋብሪካ መርቀው የከፈቱ ሲሆን ፥ በምረቃው ላይ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተገኝተዋል፡፡

 

 

በታረኩ ለገሰ

Exit mobile version