Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አሜሪካ ከውጭ ለሚገቡ መንገደኞች ያስቀመጠቸውን የኮቪድ ምርመራ መስፈርት አነሳች

አዲስ አበባ፣ሰኔ 4 ፣2014 (ኤፍ ቢሲ) አሜሪካ የአየር መንገደኞች ወደ ሀገሪቱ ከመግባታቸው በፊት የኮቪድ-19 ምርመራ ማረጋገጫ እንዲኖራቸው ያሰቀመጠችውን ህግ አነሳች።

ህጉ የተነሳው ሀገሪቱ ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል ባደረገቸው ጥረት የቫይረሱ ታማሚዎች ቁጥር ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱን ተከትሎ መሆኑን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ገልፀዋል፡፡

የሀገሪቱ የውጭ ጉዞ ኢንዱስትሪ የኮቪድ-19 ህጉ እንዲነሳ ግፊት ሲያደርግ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን፥ በተለይም ወደ አሜሪካ የሚሄዱ ሰዎች ቀድመው ቦታ ለመያዝ በመስፈርቱ ምክንያት ሲቸገሩ እንደነበር ተመላክቷል፡፡

የሀገሪቱ የበሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕክል የኮቪድ ፖሊሲ ውሳኔውን በ90 ቀናት ውስጥ እንደገና ይገመግማል የተባለ ሲሆን፥ አዲስ የኮቪድ ስርጭት  የሚስተዋል ከሆኑ እና ባለስልጣናቱ አስፈላጊ ነው ብለው ካመኑበት ህጉ ወደ ነበረበት ሊመለስ ይችላልም ነው የተባለው፡፡

አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን ለጋዜጠኞቸ በሰጡት መግለጫ “ይህንን እርምጃ መውሰድ የቻልነው ቫይረሱን ለመከላከል ባደረግነው ከፍተኛ ጥረት ነው” ብለዋል፡፡

ህይወት አድን የሆኑ ክትባቶችን እና ህክምናዎችን በስፋት ተደራሽ አድርገናል ያሉት ባለስልጣኑ፥ እነዚህ ክትባቶች እና ህክምናዎች የቫረሱን ህመም እና ሞቶች እያሰቀሩ ነው ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version