የሀገር ውስጥ ዜና

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት  በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ያስገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

By Mekoya Hailemariam

June 11, 2022

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት  በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ያስገነባው የረገ ኤያት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ተመረቀ።

ትምህርት ቤቱን ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው  እና የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ መርቀውታል።

ትምህርት ቤቱ በውስጡ 10 የመማሪያ ክፍሎች ፣ ቤተ -ሙከራ፣ ቤተ-መጻሕፍት፣ የተማሪ ክሊኒክ ፣ የአስተዳደር ሕንጻና የስብሰባ አዳራሽን ያካተተ ነው ።

የትምህርት ቤቱ መገንባት የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ከማስቻሉም በተጨማሪ ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ሆነው እንዲማሩ እድል በመፍጠር  መጠነ ማቋረጥ እንዲቀንስ እንደሚያስችል በምረቃው ላይ ተመልክቷል።