አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲሱ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት ሶማሊያ ሞቃዲሾ ገቡ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተመራው የልዑካን ቡድን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ይገኙበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሶማሊያ ቆይታቸው በፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ በዓለ ሲመት ላይ ንግግር እንደሚያርጉም ተጠቁሟል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ ጋር እና በበዓለ ሲመቱ ከሚታደሙ የሌሎች ሀገራት መሪዎች ጋር የሁለትሽ ምክክር እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተጨማሪም የጅቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ እና የኬንያው ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታም ሞቃድሾ ገብተዋል።
በአልአዛር ታደለ